ሕብረት ባንክና አዱሊስ የማማከር አገልግሎት (Adulis Consultancy ) የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
ሕብረት ባንክና አዱሊስ የማማከር አገልግሎት (Adulis Consultancy) አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ የስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዷለም ሀይሉ እና የአዱሊስ የማማከር አልግሎት (Adulis Consultancy) ዋና ሥራ አስፈፃሚና የድርጅቱ መስራች አቶ ሱፊያን ሱልጣን ናቸው፡፡
በስምምነት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ እና የአዱሊስ የማማከር አልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!