ሕብረት ባንክ ለሴት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ

ሕብረት ባንክ የኢትዮጵያ የስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ከሚያዚያ 24-25 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሴት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ባዘጋጀው የሥልጠና መርሃ-ግብር ላይ ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በሕብረት ባንክ ዋና መስርያ ቤት አዳራሽ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በዚሁ ስልጠና ስለ ሪቴይል ባንኪንግ፣ ስለብድር አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት፣ ስለስጋት አስተዳደር/Risk Management/ እና ኢንሹራንስ፣ ስለፋይናንሽያል ስቴትመንት አያያዝ እንዲሁም በመልቲ-ቻናል ባንኪንግ፤ ሕብር ኢ-ኮመርስ፣ ሕብር ሞባይል እና ኦንላይን ባንኪንግ ዙሪያ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገርም በዲጂታል ፋይናንስ ዙሪያ ለሰልጣኞች ስልጠና ተስጥቷል፡፡

በስልጠናው መዝጊያ ላይ የሕብረት ባንክ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝደንት፣በኢትዮጵያ የዩኤንሲዲኤፍ (UNCDF) አስተባባሪ የተገኙ ሲሆን ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞችም የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts