eder-and-senior-launching-1

ሕብረት ባንክ “ሕብር ዕድር”  እና  “ሕብር ለታላላቆች” የተሰኙ አዳዲስ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀመረ

eder-and-senior-launching-7

ሕብረት ባንክ "ሕብር ዕድር"  እና  "ሕብር ለታላላቆች" የተሰኙ አዳዲስ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን   በይፋ አስጀመረ

ሕብረት ባንክ  "ሕብር ዕድር" እና "ሕብር ለታላላቆች" የተሰኙትን አዳዲስ የቁጠባ የባንክ አገልግሎቶች ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በሕብር ታወር የባንኩ ዋና መስርያ ቤት በይፋ አስጀምሯል፡፡

ዕድሮችን እና የእድሜ ባለጸጋዎችን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ በጥናት የተዘጋጁት "ሕብር ዕድር" እና "ሕብር ለታላላቆች" የተሰኙት አገልግሎቶች ይፋ የተደረጉበት ይህ መርሃ ግብር በአባቶች ምርቃት ተጀምሯል፡፡ 

የባንኩ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌረዳ ተስፋዬ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት እድሮች በደስታም ሆነ በሀዘን ጊዜ አብሮነታችንን የምንገልፅባቸው፣ የምንተሳሰብባቸው፣ ደጉንም ክፉውንም ጊዜ በሕብረት ሆነን የምናልፍባቸው እና ዘመን የማይሽራቸው ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን መሆናቸውን ገልጸው ባንኩ ለዕድሮች እና ለአባላቶቻቸው እንዲሁም ለእድሜ ባለጸጋዎች የሚመቹ የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ትኩረት በመስጠት በቀጣይነትም በይበልጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ዕድሮች ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ታምራት ገ/ማርያም በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ስላቀረባቸው አዳዲስ አገልግሎቶች እና ከእድሮች ጋር አብሮ ለመሥራት ስላሳየው ቁርጠኝነት አመስግነው በቀጣይም አባላትን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ከባንኩ ጋር አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ሕብር ዕድር የቁጠባ ሒሳብን እና ከስልሳ አመት በላይ ለሆኑ ጡረተኛ የእድሜ ባለፀጋዎች በልዩነት የቀረበውን ሕብር ለታላላቆች የቁጠባ አገልግሎቶች በተመለከተ ሰፊ መግለጫ /Presentation/ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም ከታዳሚዎች ለተነሱ  ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ዕድሮች ም/ቤት  ሰብሳቢ እና የዕድር አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ የአረጋዉያን እና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር የቦርድ ፕሬዚደንት እና አባላት  ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts