ሕብረት ባንክ ሴቶችን ለማብቃት በዩናይትድ ኔሽን ዉሜን (UN Women) የተዘጋጀውን ሰነድ ፈረመ

ሕብረት ባንክ በዩናይትድ ኔሽን ዉሜን (UN Women) አዘጋጅነት ዉሜን ኢኮኖሚኪ ኢምፓወርመንት (Women Economic Empowerment) በሚል መሪ ቃል መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፏል፡፡ በኘሮግራሙ ላይም ሴቶችን ማብቃት በሚቻልባቸው መንገዶች እንዲሁም በሂደቱም የሚገጥሙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎቻቸውን በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ እንደገለፁት ሴቶችን የማብቃት ጥረት ከተማን ብቻ ሳይሆን በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙትን ሴቶችንም ለማደገፍ ሰፋ ባለ ሁኔታ የሁሉም አካላት ርብርብ የታከለበት ሥራ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

ሕብረት ባንክም በበኩሉ ሴት ሰራተኞቹን ለማብቃት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ረገድ 42.11 በመቶ የሚሆኑት የባንኩ ሠራተኞች ሴቶች መሆናቸውን እና ከአጠቃላይ የባንኩ ሠራተኞች 25 በመቶ የሚሆኑት በዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፎች በአመራር ደረጃ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ሕብረት ባንክ ለሕብረተሰቡ በሚያቀርበው የባንክ አገልግሎት ስትራቴጂና ፖሊሲዎችን በመቅረፅ ለሴቶች የተለየ ትኩረት በመስጠት የሴቶችን የፋይናንስ አቅም በይበልጥ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts