ሕብረት ባንክ በ2023/24 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 3.08 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለጸ።
የሕብረት ባንክ ባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሳቢ ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ ባለፈው በጀት አመት አለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ባንኩ በሁሉም የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀው ከታክስ በፊት 3.08 ቢሊዮን ብር ትርፍ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡ ሰብሳቢዋ አያይዘውም በበጀት ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 74.65 ቢሊዮን ብር መድረሱንና የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ወደ 7 ቢሊዮን ብር ማደጉን ገልጸዋል።
ሕብረት ባንክ ከዘመናዊና ምቹ የባንክ አገልግሎቱ ባሻገር የኮርፖሬት ማሕበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ የሚገኝ መሆኑና ባለፈው በጀት አመትም ለ19 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ20.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ በጉባኤው ተጠቅሷል።
በቀጣይም ባንኩ ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በጽናት ተቋቁሞ በፋይናንስ ሴክተሩ ያለውን ከፍተኛ ፉክክር በድል ለመሻገር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!