ሕብረት ባንክ አመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔውን አካሄደ

ሕብረት ባንክ የ2022/2023. አመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔውን “Grow your Branch, Glow you Hibret to Greatness” በሚል መሪ ቃል የባንኩ ዲሪክተሮች ቦርድ አመራርአባላት፣የባንኩ የስራአመራሮች፣የዋናው መስርያ ቤትና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት ከሐምሌ 26-27 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተርሌግዤሪ ሆቴል አከናውኗል፡፡

በጉባዔው ላይ የ2022/2023 የበጀት ዓመት ዕቀድ አፈፃፀም ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የቀጣይ ዓመትዕቀድም ለተሳታፊዎች ቀርቦ ወይይት ተካሂዶበታል፡፡ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ያሳዩቅርንጫፎችም በጉባዔው ማጠናቀቀያ ላይ ሽልማት ያገኙ ሲሆን በዚህ ጉባዔ በተምሳሌትነት ለረዥምዓመታት ያገለገሉት የባንኩ ባለውለታ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ደበበ ታከለ በደማቅ ሁኔታ ምስጋና እና ሽልማትተበርክቶላቸው በባንኩ የበላይ አመራሮች የክብር ካባ ተደርቦላቸዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!

Similar Posts