ሕብረት ባንክ እና ኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኤል.ኤል.ፒ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ሕብረት ባንክ እና ኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኤል.ኤል.ፒ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ እና የኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኤል.ኤል.ፒ ማኔጂንግ ፓርትነር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ፈቃዱ ናቸው፡፡ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት የፋይናንስ ተጠቃሚዎችን በተሻለ ብቃት ለማገልገል እና ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችል ነው፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts