ሕብረት ባንክ እና ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ፒ.ኤል.ሲ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ሕብረት ባንክ እና ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ፒ.ኤል.ሲ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ መጋቢት 08 ቀን 2015 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መሥርያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ እና የኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ፒ.ኤል.ሲ ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፈቃድ ጌታቸው ናቸው፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት የባንኩን ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና ተደራሽነቱንም ለማስፋት የሚያስችል ነው፡፡ ሕብረት ባንክ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት የታገዘ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ ባንክ ነው፡፡ በመሆኑም ከተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በጋራ በመስራት ለደንበኞቹ ቀላልና ምቹ አገልግሎቶችን እያቀረበ ይገኛል፡፡ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ፒ.ኤል.ሲ ጋር የተደረሰው ስምምነትም ይህንኑ ተግባር የሚያጠናክር ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts