ሕብረት ባንክ እና የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር በጋር ለመስራት ተስማሙ፡፡

ሕብረት ባንክ እና የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር በጋር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ህዳር 30 2015 ዓ/ም ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ እና የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚደንት ወ/ሪት ሳሚያ አብዱልቃድር ናቸው፡፡ በስምምነቱ ወቅት የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ እንደገለጹት ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታት እና መደገፍ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዚህ ላይ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚደንት ወ/ሪት ሳሚያ አብዱልቃድር በበኩላቸው ሕብረት ባንክ በራሱ ተነሳሽነት ማህበሩን ቀርቦ በማናገር እና አጋር በመሆን የመጀመሪያው ባንክ መሆኑን አድንቀው ስምምነቱ ብዙ አበይት ሥራዎችን በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሰረት የጣለ ነው ብለዋል፡፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ከማበረታታት ባሻገር የሁለቱን ተቋማት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያጐለብት ነው፡፡

Similar Posts