ሕብረት ባንክ እና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የሀገራችንን ስምና ባንዲራ ከፍ በማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የልብ ኩራት  በሆኑ አትሌቶች የተቋቋመ ድረጅት ሲሆን አላማውም በተለያዩ ጊዜያት ሀገራችንን በክብር ያስጠሩና በአሁን ወቅት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የሀገር ባለውለታ አትሌቶችን መደገፍ ነው፡፡

የጋራ ስምምነቱ ዓላማ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በሕብረት ባንክ በኩል እንዲያከናውን እና ሕብረት ባንክም ዘርፈ ብዙ የሆኑ የባንክ አገልግሎቶችን ለድርጅቱ፣ ለሠራተኞቹ እና ለአባላቱ ለማቅረብ ብሎም በተለያዩ ጊዜያት ሀገራችንን በክብር ያስጠሩና በአሁኑ ወቅት  ድጋፍን የሚሹ የሀገር ባለውለታ አትሌቶችን ለማገዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መደገፍ ነው፡፡   

በዚህም ረገድ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት  የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ/ም 100 ለሚደርሱ አንጋፋ አትሌቶች በጃንሜዳ  የማዕድ ማጋራት መርኃ-ግብር የሚያከናውን ሲሆን ሕብረት ባንክም ለዚህ ዝግጅት ስፖንሰር ሆኗል፡፡   በቀጣይም የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ሕብረት ባንክ በትብብር መንፈስ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ሕብረት ባንክና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለመላው የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች መልካም የፋሲካ በዓል አንዲሆን ይመኛሉ!

Similar Posts