Hibret-Bank-IFB-Awarness-Campagin-Jimma-Region-1

ሕብረት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሀገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩን በይፋ አስጀመረ፡፡

ሕብረት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሀገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩን በይፋ አስጀመረ፡፡

ሕብረት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሀገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩን ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ኃይሌ ሪዞርት ሆቴል አስጀምሯል፡፡

የመርሃ ግብሩ መክፈቻ ሥነስርዓት በአባገዳዎች እና በአካባቢው ዑለማዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የጅማ ከተማ የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሐመድ አሚን የክብር እንግዳ በመሆን ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡    

በመቀጠልም ከመድረክ በሕብረት ባንክ የሸሪዓ ቦርድ አማካሪዎች እና በባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተ/ቺፍ ኦፊሰር የተመራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከታዳሚው ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በመክፈቻ ሥነስርዓቱ ማጠቃለያ ላይ የሕብረት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተ/ቺፍ ኦፊሰር አቶ አልፈሬድ በረካ እንደተናገሩት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩ በቀጣይ በጅማ እና በአካባቢዋ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ተደራሽ ባልሆነባቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ 5 ሚሊዮን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት እንደ ከዚህ ቀደሙ ለማድረስ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ይህ የባንክ አገልግሎት አዳዲስ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የተናገሩ ሲሆን በዚህ ረገድ መርሃ-ግብሩ በተለይም ሴቶችን ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እና በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸውን ጉልህ ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡  

በዝግጅቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጅማ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ኃላፊ፣ የጅማ ከተማ ንግድ ዘርፍ ማህበር ተወካይ፣ የጅማ ከተማ ሴቶች ቢሮ ተወካይ፣ የኤፍ.ኤስ.ዲ ኢትዮጵያ (FSD Ethiopia) ተወካይ፣ የአካባቢው ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሮችን ማካሄዱ ይታወቃል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts