ሕብረት ባንክ የደንበኞች አገልግሎትና የምስጋና ሳምንት ፕሮግራም አስጀመረ

ሕብረት ባንክ ለክቡራን ደንበኞቹ ከሀምሌ 03 እስከ ሀምሌ 08 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት መርሀ ግብር አስጀመረ ፡፡ የመርሀ ግብሩ ዋና አላማ ክቡራን የባንኩ ደንበኞችን ለማመስገን እና እውቅና ለመስጠት ነው፡፡

የመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ በሕብር ታወር ቅርንጫፍ የተከናወነ ሲሆን መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ደንበኞችን ማመስገንና እውቅና መስጠት ሊበረታታ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በዚሁ ስነ-ስርዓት ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በቅርንጫፉ በመገኘት አገልግሎትና ለደንበኞች እውቅና ሰጥተዋል፡፡

የሕብረት ባንክ የደንበኞች ሳምንት በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

customerservice #customersatisfaction #Ethiopia

Similar Posts