ሕብረት ባንክ የ2ተኛውን ዙር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎችን ሸለመ፡፡

ሕብረት ባንክ የ2ተኛውን ዙር “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” መርሃ ግብር  የሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎችን ሸለመ፡፡

ሕብረት ባንክ ለአምስት ተከታታይ ወራት ባካሄደው የ‹‹ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ›› መርሐ ግብር እጣ የወጣላቸውን ባለዕድለኞች ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በዋናው መስርያ ቤት ሸልሟል፡፡

በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ ዋና ስራአስፈጻሚ  አቶ መላኩ ከበደ ባደረጉት ንግግር ሕብረት ባንክን አምነው በባንኩ የቆጠቡና የመነዘሩ የባንኩ ደንበኞችን አመስግነው የባንኩ ጉዞ ከደንበኞች ጉዞ የባንኩ ስኬትም ከደንበኞች ስኬት ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል ገልጸዋል፡፡

በሽልማቱ አንድ (1) ሱዙኪ ዲዛየር አውቶሞቢል፣ ሁለት (2) ባለ ሶስት እግር ባጃጆች)፣ ሶስት (3) ስማርት ቴሌቪዢኖች፣ ሶስት (3) ፍሪጆች፣ ሶስት (3) የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እና ሶስት( 3) የዉሀ ማጣሪያ ማሽኖች ለእድለኞች የተበረከቱ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ እድለኞችም በተመሳሳ በባንኩ የክልል ቅርንጫፎች ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡  

ሕብረት  ባንክ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግ ብሎም የባንኩን የተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግ አልሞ  ከታህሳስ 6 እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2014 ዓ/ም ያዘጋጀው የ”ይቆጥቡ፤ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ“ መርሃ ግብር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ሰኔ 02 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ መከናወኑ ይታወሳል፡፡

#HibretBank #ሕብረትባንክ

Similar Posts