ሕብረት ባንክ “ጥላ ፕሮጀክት” በተሰኘው የብድር አገልግሎት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውውይት መድረክ አከናወነ፡፡

ሕብረት ባንክ "ጥላ ፕሮጀክት" የተሰፕውንና ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከእልባት ማኔጅመንት ቴክኖሎጂ እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን በመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ያልተካተቱ የማሕብረሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር የውውይት እና የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ አከናውኗል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የባንኩ ም/ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዷለም ሐይሉ እንደገለፁት ሕብረት ባንክ የፋይናንስ አቅርቦት ያልተመቻቸላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለብድር ማስያዣ የብድር አቅርቦት ያመቻቸ የመጀመሪያው ባንክ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የጂማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ዋሴ ግርማ የሕብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እና የሥራ ቦታን በመስጠት የከተማው አስተዳደር አብሮ እየሰራ ያለ ሲሆን ለወደፊትም ለሚኖር ተጨማሪ የመስሪያ ቦታ ጥያቄዎችን በመፍታት አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮጀክቱ ከየት ወዴት የሚለውን የሚያሳይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከሆኑ አባላት በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts