በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ሕብረት ባንክ ላደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ

ሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ አንዱ ሲሆን የድርጅቱ አመራሮች በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ባንኩ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ የተበረከተውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡

ሕብረት ባንክ ከዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts