ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር ሕብረት ባንክ ላደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ
ሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር አንዱ ሲሆን የድርጅቱ መስራቾችና አመራሮች በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ባንኩ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የሕብረት ባንክ ቢዝነስ እና ኦፕሬሽንስ ዘርፍ ሲኒየር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ የተበረከተውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
ሕብረት ባንክ ከዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!