ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሁሉም ባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሁሉም ባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ብሔራዊ መታወቂያን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር የተለያዩ አማራጮች ይፋ መደረጋቸው ለምዝገባው ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ያለው ባንኩ፤ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳስቧል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሀረር፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ አስተዳደር፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ፣ ሸገር፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ባቱ፣ አምቦ፣ መቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ጋር ማስተሳሰር አለባቸው ብሏል።
በተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ነው ያለው።
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ጋር የማያስተሳስሩ ደንበኞች ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የሚታገድ መሆኑን ገልጾ፤ እገዳው የሚነሳው የሂሳብ ቁጥሩ ከፋይዳ ጋር ሲተሳሰር ብቻ ነው በማለት አሳስቧል፡፡
ስለሆነም እርስዎም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም በድረ-ገፅ https://services.hibretbank.com.et/fayda የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (FAN) ተጠቅመው የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!