እንኳን ደስ አለን! ሕብረት ባንክ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆኑ የልዩ ተሸላሚ እና የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማቶችን ተቀበለ

እንኳን ደስ አለን! ሕብረት ባንክ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆኑ የልዩ ተሸላሚ እና የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማቶችን ተቀበለ

ሕብረት ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች እውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ላይ የ2016 ዓ.ም የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋይ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ በተከታታይ አራት አመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ በመሆኑ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ባንኩ ያገኛቸውን ሽልማቶች የባንኩ ተ/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል፡፡

ሕብረት ባንክ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ ላይ በታማኝነት ግብር በመክፍል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ሽልማቱም ለዚህ ተግባር እውቅና የሠጠ ነው፡፡

ሽልማቶቹ የሁላችንም ያላሰለሰ የጥረት ውጤት በመሆናቸው ለሕብረት ባንክ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አለን!
¬
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ መረጃዎች እንዲደርስዎ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡ linktr.ee/Hibret.Bank

Similar Posts