ወቅታዊ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እና ስርጭትን በተመለከተ ከሕብረት ባንክ የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ 3ዐ ቀን 2ዐ17 ዓ.ም.

ሕብረት ባንክ ባሳለፍነው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ 4ዐ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለደንበኞቹ አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም በዛሬው ዕለት 5 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለደንበኞቹ ፈቅዷል፡፡ የውጭ ምንዛሬ አደላደሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ባንኮች ለአስፈላጊ ግብዓቶች እና ለወሳኝ የአገልግሎት ክፍያዎች ቅድሚያ እንዲሰጡ በሚያዘው መሠረት የተከናወነ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ለነዳጅ እንዲሁም ለሌሎች ስትራቴጂያዊ ምርቶች የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እና ስርጭቱን በፍትሐዊነትና በግልጽነት አከናውኗል፡፡

በቀጣይም ሕብረት ባንክ የብሔራዊ ባንክን መመሪያ መሠረት ባደረገ መልኩ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እና ስርጭትን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰራ ለክቡራን ደንበኞቹ ከወዲሁ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts