የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥሮች 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
| ተራ ቁ. | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1. | አቶ ብርሃኑ በላይ መኳንንት | አቶ ብርሃኑ በላይ መኳንንት | አብነት | ሞጆ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 160 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | 344/07 | 1,643,980.00 | ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 2. | አቶ ፈንታሁን በዜ ሽፈራው | አቶ ፈንታሁን በዜ ሽፈራው | ሞጣ | ጎጃም፣ሞጣ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | 2391/2015 | 5005/2013 | ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 3. | ወ/ሮ እየሩስ ገዳሙ አየለ | አቶ አበባው ዓለም ገድፍ | ፈለገ ህይወት | ጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 05፣የቦታ ስፋት 150 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | ከአገ/113207/13 | 1,332,915.00 | ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| አቶ አበባው ዓለም ገድፍ | ፈለገ ህይወት | ሞጆ | ጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 05፣የቦታ ስፋት 150 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | ከአገ/113208/13 | 1,278,908.00 | ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡በተራ ቁጥር 2 የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው ባህርዳር ከተማ፣ዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ፣ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ከተራ ቁጥር 3-7የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ ጎንደር ከተማ በሚገኘው የባንኩ ፋሲል ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶችለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አብነት ቅርንጫፍ፡ 011 2 73 55 81፣ ሞጣ ቅርንጫፍ፡ 058 661 19 48፣ ገንደውሃ ቅርንጫፍ: 058 331 05 55፣ ደባርቅ ቅርንጫፍ፡ 058 417 36 67 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!