የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
| ተራ ቁ. | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሽከርካሪ አይነት | የስሪት ዘመን | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ተ.ዕ.ታ. ሳይጨምር) | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1. | ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | መሐል አራዳ | አአ-03-A53273 | አነስተኛ የሕዝብ- ኮሪያ ሀዩንዳይ | 2014 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር | KMHWG81R7EU621989 | G4KG-DA3874 43 | 1,530,000.00 | ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተሽከርካሪውን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
- የተሽከርካሪው ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር +251 11 470 0315/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!