HibretBank Customer Engagement Hosaana 01

የሕብረት ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራር በሆሳዕና ከተማ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ።

የሕብረት ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራር በሆሳዕና ከተማ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ።

የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ከፍተኛ አመራሮች በሆሳዕና ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች፣ ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ ከተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ልዩ የውይይት መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማሳደግ፣ የደንበኞችን ቁጥር ለማብዛት እና በአካባቢው የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶችን አጠናክሮ ለማስጠቀል በሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር ለአካባቢው ኢኮኖሚሚያዊ ዕድገት እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን  እና ወደፊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥልበት መንገድ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገብረእግዚአብሔር እና የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና መብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙአል ሽጉጤ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የሕብረት ባንክ የበላይ አመራሮች ከደንበኞች ጋር እንዲህ ዓይነት ውይይት በቅርብ እና በአካል ማድረጋቸው በባንኩ እና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts