የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ በ6ኛው ዙር የዘለላ ፕሮጀክት የምክክር መድረክ ላይ ልምዳቸውን አካፈሉ
የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ "Power up Capacity and Connectedness" በሚል ርዕስ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው የ6ኛው ዙር የዘለላ የትስስርና እና የፖሊሲ አድቮኬሲ መድረክ ላይ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
አቶ መላኩ በንግግራቸው የፈጠራ ስራ ሀሳቦች በሀገር ደረጀ ትልቅ ለውጥ እንዲያመጡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡ በመንግስት ደረጃ አስፈላጊው የሕግ ማዕከፍ ተዘጋጅቶ፣ ሥራ ፈጣሪዎችም የፈጠራ ሀሳቸውን ለገበያ በሚቀርብ ሁኔታ ቀርፀው፣ የፋይናንስ ተቋማትም በበኩላቸው የቀረበውን ሀሳብ ዋጋ በመረዳት እና ሀሳቡን ፋይናንስ በማድረግ በሕብረት ትልቅ ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
ሕብረት ባንክ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ቁርጠኛ መሆኑን እና በዚህ አንፃርም ባንኩ በውስጥ የቴክኖሎጂ ሠራተኞቹ በቅርቡ ያስተዋወቀው የሕብር ሞባይል አገልግሎት ጨምሮ የተለያዩ ሲስተሞችን በውስጥ አቅም ማበልፀጉ እንደ አንድ ተሞክሮ የሚታይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳትፊዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!