የሕብረት ባንክ ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በ2025/26 በጀት ዓመት ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎቹ ዕውቅና ሰጠ::















የሕብረት ባንክ ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በ2025/26 በጀት ዓመት ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎቹ ዕውቅና ሰጠ::
የሕብረት ባንክ ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የ2025/26 በጀት ዓመት በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዲስትሪክቱ ቅርንጫፎች በኤደን ገነት መናፈሻ አዳራሽ ባዘጋጀው የምሳ ግብዣ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡
ዲስትሪክቱ ባዘገጀው የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በዲስትሪክቱ ሥር የሚገኙ ቅርንጫፎች እና ከፍ ያለ አጋርነት በማሳየታቸው በቅርንጫፎች የተጋበዙ ደንበኞች እንዲሁም የባንኩ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተው በዓመቱ ላበረከቱት ድጋፍ እና አስተዋጽኦ ከዲስትሪክቱ ከፍ ያለ ምስጋና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሕብረት ባንክ በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም. ባዘጋጀው የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ የአንደኛ ደረጃ ተሸለሚ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!