የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሕብረት ባንክ አክስዮን ማህበርን የምዝገባ መግለጫ አጸደቀ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሕብረት ባንክ አክስዮን ማህበርን የምዝገባ መግለጫ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. አጽድቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በነባር ባለአክስዮኖች የተያዙ 11,665,497 (አስራ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሰባት) ነባር አክስዮኖችን ምዝገባ ማጽደቁን  በይፋ አሳውቋል፡፡

ምዝገባው መጽደቁን ተከትሎ ባንካችን የደንበኞች ሳቢ መግለጫን (Prospectus) እና ሌሎች ተዛማጅ ሠነዶችን በባንኩ ድረ ገጽ [https://www.hibretbank.com.et/about/prospectus] ላይ ይገኛል፡፡

በባለስልጣኑ የወጣው መግለጫ ሠነደ ሙዓለ ንዋዮች በባለሥልጣኑ መመዝገባቸውን ለሕዝብ ለማሳወቅ ብቻ ሲሆን፣ ማንኛውንም ሠነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመሸጥ የቀረበ ጥያቄ፣ እንዲገዙ የተሰጠ ድጋፍ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ ወይም ማስታወቂያ አለመሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts