የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሕባ007/2018

ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትናነት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

.የንብረቱ ዓይነትየቦታው ስፋትየንብረቱ የይዞታ ማረጋገጫንብረቱ የሚገኝበት ከተማንብረቱ የሚገኝበት ቀበሌንብረቱ የሚገኝበት የቤት ቁጥርየጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
1መኖሪያ ቤት504241449/2002ጋምቤላ ከተማ04አዲስ 633,075.00
2መኖሪያ ቤት190ከአገ/112504/12አዴት ከተማ01አዲስ 1,474,417.00
3መኖሪያ ቤት65628649/05ጋምቤላ ከተማ05አዲስ 5,440,260.00
4መኖሪያ ቤት200ወከ/በኩ/ክ/ከ/ማ/1132/06ወልቂጤ ከተማ፣ በኩር ክ/ተማ አዲስ 6,810,509.00
5መኖሪያ ቤት72ቦሌ 10/25/6/1/28878/00አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ10አዲስ 11,616,516.00
6መኖሪያ ቤት206.352172/222ሀዋሳ/ቱላ ክ/ከተማ01አዲስ 4,047,570.00
7መኖሪያ ቤት200WBIFL/9998/2014ሆለታ ከተማገልገል ኩዬአዲስ 2,252,594.00
8መኖሪያ ቤት330AA00051105530አዲስ አበባየካ ወረዳ 11አዲስ 43,060,748.00
9መኖሪያ ቤት230AA000051104797አዲስ አበባ፣ የካ ክ/ከተማ 11አዲስ 37,732,999.00
10መኖሪያ ቤት180BH/1622/M.1125/2014ቡሌ ሆራ ከተማ ቀበሌ B/Qቡሌ ሆራ ከተማ ቀበሌ B/Qአዲስ 2,367,141.00
11መኖሪያ ቤት14017827በሻሸመኔ ከተማ መልካ አዲስ  3,037,102.23
12መኖሪያ ቤት230AA000051104797ስርባ ክ/ከተማ "አለሉአዲስ 2,083,442.00
13ፋብሪካ500ኢፓልኮ/ጎን/82/12ጎንደር አዲስ29,212,988.00
14ለኢንዱስትሪ አገልግሎት10,0000160/2011አማራ ክልል ገንደውሃ ከተማ02አዲስ 9,000,000.00
15የሚውል ለምግብ ዘይት5,000ኢፓልኮ/ጎን/ሊ/54/2012አማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ02አዲስ 28,681,501.00

በመሆኑም

  1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተገለጹት አድራሻዎች በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን ይህ ሳይገለጽ ቢቀር ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ባንኩ ተጨማሪ 15% ተ.እ.ታን በመደምር የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
  4. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ደግሞ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  5. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 09፡30 ሰአት በዋናው መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ ካፍቴሪያ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ባንኩ ንብረቶቹን በገዢው ስም ለማዘዋወር ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 10 24 ወይም 0114 16 97 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts