የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማ/ ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግ/ማ/ሸገርአዲስ አበባ ከተማ፣አራዳ ክ/ከተማ፣ወረዳ 09፣የቦታ ስፋት 852.6 ካ.ሜ አገልግሎት ለድርጅት የሆነ በግንባታ ላይ ያለ G+7 (ባለሰባት ፎቅ ሕንፃ)፤  
አ/ሊዝ/17/08/6362/01
 
355,897,544.00
ኅዳር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2.አቶ ዳግም ከበደ ከቻራዶ/ር ከበደ ከቻራ ሸዋዓለም ባንክአዲስ አበባ፣ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 06፣የቦታ ስፋት 667 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለድርጅት (ንግድ)የሆነ G+ 6 ሕንፃ፤AA000060603587 
123,911,020.00
ኅዳር 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
3.አቶ አረጋ እንድሬ አለማውአቶ አረጋ እንድሬ እና ወ/ሮ ፈለቁ ደምሴኮተቤአዲስ አበባ ከተማ፣የካ ክ/ከተማ፣ወረዳ 09፣የቦታ ስፋት 191 ካ.ሜ የሆነ ለመኖሪያ አገልግሎት የሆነ ሰርቪስ ያለው G+2 (ባለሁለት ፎቅ) ቤት፤  
AA000050901646
19,012,714.00ኅዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም  ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
4.ባርሳቤ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ/መብቶም ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቃሊቲ አዲስ አበባ ከተማ፣አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ወረዳ 05፣የቦታ ስፋት 1942 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለኢንደስትሪ የሆነ ቤት 
አቃ/ቃ/ክ/ከ/ሊዝ/ጨ/062/2
 
23,965,040.00
ኅዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5:00 እስከ 6:00 ሰዓት
5.ወ/ሮ አሳቤ ጫኔ ይርዳዉወ/ሮ አሳቤ ጫኔ ይርዳዉቃሊቲኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ፣ሱሉልታ ክ/ከተማ፣ወረዳ QW ፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤትSul/1916/153,658,755.00ኅዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
6.አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድአቶ ነሻ አህመድ አልይሕብር ታወርአዳማ ከተማ፣ቀበሌ 03፣የቦታ ስፋት 1709 ካ.ሜ የሆነ ለመጋዘን አገልግሎት የሚውል 2110/200017,183,808.00ኀዳር 16 ቀን 2018  ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
7.ኔይሎስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግ/ማ/ኔይሎስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቦምብ ተራባህርዳር ከተማ፣ዳ/ሚኒሊክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14(ግንቦት 20) የቦታ ስፋት 15,000 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለኢንደስትሪ የሆነ ህንፃ፤ባህኢፓ/0162/11 
13,848,880.00
ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
8.አቶ አዲሱ አላምኑ ካሳ አቶ አዲሱ አላምኑ ካሳእንጅባራእንጅባራ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 201.972 ካ.ሜ፣ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤትAM0100116050262,180,981.00ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት
9.አቶ አደራጀው ታረቀኝ ጎሸአቶ አደራጀው ታረቀኝ ጎሸፋሲልጎንደር ከተማ፣አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 19፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ የሆነ፣ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት 
9903/06
6,421,513.00ኅዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  3. ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ ከተራ ቁጥር 5-6 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡ ከተራ ቁጥር 7-8  ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በባህርዳር ከተማ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና (ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በተራ ቁጥር 9 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው ጎንደር ከተማ በሚገኘው የባንኩ ፋሲል ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ 
  4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  8. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡ ሸገር ቅርንጫፍ፡ 011 126 54 62፣ አለም ባንክ ቅርንጫፍ፡ 011 369 47 79፣ ኮተቤ ቅርንጫፍ: 011 667 52 54፣ ቃሊቲ ቅርንጫፍ፡ 011 462  62 01፣ ሕብር ታወር ቅርንጫፍ 011 557 54 47፣ ቦምብ ተራ ቅርንጫፍ፡ 011 278 17 28፣ እንጅባራ ቅርንጫፍ፡ 058 227 18 22፣ ፋሲል ቅርንጫፍ፡ 058 111 68 70 ወይም የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ  011 470 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts